ኢትዮጵያ የብዝሃ ሕይወት ሀበቷን ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
20:35 18.08.2026 (የተሻሻለ: 20:44 18.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የብዝሃ ሕይወት ሀበቷን ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀመረች
የዱር እንስሳትን መጠበቅ እና የተራቆቱ ሥነ-ምህዳሮችን የመመለስ ግብ ያነገበ የ12 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ይፋ ተደርጓል
ፕሮጀክቱ እ.ኤ.አ እስከ 2033 ድረስ ለሰባት ዓመታት ይቆያል፡፡
ስለፕሮጀክቱ ቁልፍ ነጥቦች፦
▪ የተበላሹ ሥነ-ምህዳሮችን መልሶ ማቋቋም፣
▪ ሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት ዝውውርን መግታት፣
▪ አካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታዩ የፋይናንስና የሥራ አቅም ክፍተቶችን መሙላት።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ፤ “የዱር እንስሳትና መኖሪያዎቻቸው በእርሻ መስፋፋት፣ በደን ጭፍጨፋ፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በመሬት አጠቃቀም ችግር፣ በሕገ-ወጥ አደን ንግድ እንዲሁም እየጨመረ በመጣው የሰውና የዱር እንስሳት ግጭት ምክንያት ለከፍተኛ ጫና ተዳርገዋል” ማለታቸውን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X