የአዲስ አበባን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በቀን በ60 ሺህ ሜትር ኪዩብ የሚያሳድግ አዲስ ፕሮጀክት ተመረቀ

ሰብስክራይብ

የአዲስ አበባን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በቀን በ60 ሺህ ሜትር ኪዩብ የሚያሳድግ አዲስ ፕሮጀክት ተመረቀ

ከንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በተጨማሪ በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የኮዬ ዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያም ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

ቁልፍ ነጥቦች፦

ከ5 ዓመታት በፊት በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ የነበረው የከተማዋ የውሃ አቅርቦት፤ በለገዳዲ፣ ቦሌ አራብሳ፣ ቱሉ ጉዶ እና በረከት በተካሄዱ የከርሰ ምድር ውሃ ልማቶች አሁን 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ደርሷል።

በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው የከተማዋ ፍሳሽ የማጣራት አቅም አዲሱን ፕሮጀክት ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ሆኗል።

በተያዘው በጀት ዓመት (2019) በቀን ተጨማሪ 130 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚያስችል ሌላ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል።

 

ፕሮጀክቱን መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0