የኢራን ጦርነት ቻይና የዓለም የነዳጅ ዋጋን እንድታረጋጋ ያደረጋት እንዴት ነው?

የኢራን ጦርነት ቻይና የዓለም የነዳጅ ዋጋን እንድታረጋጋ ያደረጋት እንዴት ነው?
የኢራን ጦርነት የሆርሙዝ የባሕር መስመርን በዘጋ ወቅት የኃይል ገበያዎች ለከፋ ሁኔታ ተዘጋጅተው ነበር። ተንታኞች የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ150 ዶላር በላይ እንደሚያሻቅብ እና ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ውድቀት እንደሚከሰት አስጠንቅቀውም ነበር።
ነገር ግን የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ተረጋግቶ ከ90 ዶላር በታች ሆኖ ቆይቷል። ለዚህ ያልተጠበቀ ውጤት ዋናው ምክንያት ቻይና በነዳጅ ገበያው ላይ ያሳደረችው ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሆነ ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል።
በዓለም ትልቋ የነዳጅ አስመጪ የሆነችው ቻይና፤ የድፍድፍ ነዳጅ ገቢያዋን በአንድ ሦስተኛ ገደማ ማለትም በቀን ወደ 3 ሚሊዮን በርሜል ገደማ በመቀነስ ለቀውሱ ምላሽ ሰጥታለች። ይህ ሆን ተብሎ የተደረገ ቅነሳ፤ ድንጋጤ በሚፈጥረው ከፍተኛ ፍላጎት ዋጋ ሰማይ እንዳይነካ በማድረግ የዓለም አቀፉ የኃይል ገበያ እንዲረጋጋ አገልግሏል።
ይህ ከፍተኛ ቅናሽ ሊደረግ የቻለው ቻይና ለዓመታት ነዳጅ ስታከማች በመቆየቷ ነው።
ግጭቱ በጀመረበት ወቅት የቻይና ስትራቴጂካዊ እና ንግድ ነክ የነዳጅ ክምችት ወደ 1.4 ቢሊዮን በርሜል ይጠጋ እንደነበር ተገምቷል። ይህም ከሁሉም 32 የዓለም አቀፍ የኃይል ኤጀንሲ አባል ሀገራት ጥምር ክምችት የሚበልጥ ነው።
🟠 ይህ ግዙፍ ክምችት ቻይና በጦርነት በናረ ዋጋ ነዳጅ መግዛት ሳያስፈልጋት የሀገር ውስጥ የነዳጅ ማጣራት ሥራዋን እንድታስቀጥል አስችሏታል።
ይህ በእንዲህ እናዳለ የቻይና የኤሌክትሪክ ኃይል እንቅስቃሴ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
◻ በ2026 ግማሽ ዓመት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በቀን የ1.4 እስከ 1.5 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ፍላጎትን ተክተዋል።
◻ አዳዲስ የኃይል አማራጭ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከአዳዲስ መኪኖች ሽያጭ ከ60% በላይ የሚሸፍኑ በመሆናቸው፤ የቻይና የትራንስፖርት ዘርፍ ለነዳጅ ዋጋ መናጋት ከፍተኛ እና እያደገ የመጣ የመቋቋም አቅም ገንብቷል።
◻ በዚህ የመዋቅራዊ ፍላጎት ቅናሽ እና የተለመዱት የነዳጅ ሞተር ተሽከርካሪዎች ሊጠቀሙት ይችል በነበረው ነዳጅ መካከል ያለው ልዩነት አሁን በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል ከሚያልፈው ነዳጅ ከአስር አንድ እጅ (1/10) ገደማ ጋር እኩል ነው።
ቻይና የድፍድፍ ነዳጅ ግዢዋን ከመቀነስ ባለፈ፤ የሀገር ውስጥ አቅርቦትን ለማረጋጋት የተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ወጪ ንግዷንም ገድባለች። ከፍተኛ ዋጋ ደንበኞችም ሆኑ የንግድ ተቋማት በነዳጅ አጠቃቀማቸው ላይ የበለጠ እንዲጠነቀቁ በማድረጉ፤ የኢራን ጦርነት የሀገር ውስጥ የቤንዚን ፍላጎት መቀነስን አፋጥኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X