የሳኅል ሀገራት ጥምረት ሕዝቦች 'የማይቀለበስ የሉዓላዊነት ውሳኔ አድርገዋል' - የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር
08:00 17.08.2026 (የተሻሻለ: 08:04 17.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ሕዝቦች 'የማይቀለበስ የሉዓላዊነት ውሳኔ አድርገዋል' - የቡርኪና ፋሶ ጠቅላይ ሚኒስትር
በመሬታቸው የሚፈፀም "ብዝበዛን" አንቀበልም፤ "የሌሎች ጥቅም አስጠባቂ አገልጋይ መሆንንም" አሻፈረን ብለዋል ሲሉ ጃን ኢማኑኤል ዋድራኦጎ በኡጋዱጉ በተካሄደው የመጀመሪያው የሳኅል የኢነርጂ፣ የማዕድን እና የፔትሮሊየም ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
ይህ አቋም በሌሎች የጥምረቱ አባል ሀገራትም ድጋፍ አግኝቷል፡-
ልማትን "የራስ" ለማድረግ ጥምረቱ "የተፈጥሮ ሀብቱን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ አለበት" ሲሉ የማሊ የማዕድን ሚኒስትር አማዱ ኬይታ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኒጀር ዓላማ ከሌሎች የጥምረቱ ሀገራት ጋር በመተባበር "የነዳጅ አቅሟን ማልማት" እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትሩ ኡስማን አባርቺ አስገንዝበዋል።
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ሚኒስትሮችን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የስፑትኒክ አፍሪካን ቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X