በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከኤሌክትሪክ ቋት ውጪ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከኤሌክትሪክ ቋት ውጪ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ተመረቁ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ እና በሀሮጉራቲ ቀበሌ አጠቃላይ ወጪያቸው 640 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት መስጠር ጀምረዋል።
የተገነቡት አነስተኛ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች 3 ሺህ 646 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ።
በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2035 70% ከግሪድ እና 30% ከግሪድ ውጪ የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ሱልጣን ወሊ ፕሮጀክቱን መርቀው ሲከፍቱ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X