የባሕር በር ማጣት ኢትዮጵያን ለከባድ እና ተደራራቢ ጫናዎች አጋልጧል - ሚኒስትር

ሰብስክራይብ
የባሕር በር እጦት ኢትዮጵያን ለከባድ እና ተደራራቢ ጫናዎች አጋልጧል - ሚኒስትር

የኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ መሆን በገንዘብ ብቻ ሊተመኑ የማይችሉ ከባድ የኢኮኖሚ፣ የሎጂስቲክ እና የስትራቴጂክ ጫናዎችን እንደፈጠረባት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልጸዋል።

በሚኒስትሩ የተነሱ ዋና ዋና ማነቆዎች፦

ከፍተኛ ወጪ፡ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለወደብ እና ተያያዥ ወጪዎች ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች።

የዲጂታል ሥርዓት ክፍተት፡ የውጭ ወደቦች ተመሳሳይ የዲጂታል ሽግግር ስላላጠናቀቁ፤ ኢትዮጵያ የገቢ እቃዎችን ለመከታተል የዘረጋችውን አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልቻለችም።

የሀብት ብክነት፡ በውጭ ወደቦች ላይ በሚደረግ የዕቃዎች አያያዝ ችግር (በማውረድ እና በመጫን ሂደት) ምክንያት እንደ ማዳበሪያ ያሉ ወሳኝ ገቢ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ብክነት ይደርሳል።

የሠራተኞች እንግልት፡ በውጭ ወደቦች ላይ የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በተደጋጋሚ ለሚገጥሟቸው የአሠራር እና የደህንነት ችግሮች የዲፕሎማሲያዊ ጣልቃ ገብነት ይጠይቃሉ።

በራስ ቁጥጥር ስር ያለ የባሕር በር ማግኘት ለእነዚህ ስር ሰደድ ማነቆዎች መፍትሄ እንደሆነ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0