ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ብሪታንያ ሠራሽ ድሮኖችን እንደምትጠቀም ታወቀ
17:51 16.08.2026 (የተሻሻለ: 18:03 16.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩክሬን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ብሪታንያ ሠራሽ ድሮኖችን እንደምትጠቀም ታወቀ
ዩክሬን በሁለት የብሪታንያ ኩባንያዎች የተሠሩ ድሮኖችን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ለሚፈጸሙ የረጅም ርቀት ጥቃቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ ማዋሏን 'ዘ ታይምስ' የዩክሬን ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የብሪታንያው ግዙፍ የመከላከያ ኩባንያ ቢኤኢ ሲስተምስ ስር በሚገኝ ኩባንያ የተገነባውን "ኒያን" ጨምሮ የብሪታንያ ድሮኖች፤ ላለፉት ስድስት ወራት ያህል በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች እንዲሁም በሩሲያ ግዛት ጥልቅ ክፍሎች ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ላይ ተሳትፈዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ሩሲያ በዩክሬን ውስጣዊ ክፍል የምታካሂደው የአጸፋ ጥቃት እጅግ የበረታ እና ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ሞስኮ የምዕራባውያን የጦር መሣሪያ አቅርቦት የሰላም ጥረቶችን እንደሚያደናቅፍ እና ኔቶን የግጭቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ የሚያደርግ ነው ስትል ትገልጻለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X