የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የብቁ አመራሮች ምንጭ መሆኑን ቀጠለ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የብቁ አመራሮች ምንጭ መሆኑን ቀጠለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የብቁ አመራሮች ምንጭ መሆኑን ቀጠለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 16.08.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የብቁ አመራሮች ምንጭ መሆኑን ቀጠለ

55% በዛምቢያ መንግሥት እና 45% ደግሞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተያዘው የዛምቢያ አየር መንገድ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈፃሚ የነበሩትን እና ከ19 ዓመታት በላይ የአቪዬሽን ልምድ ያካበቱትን አማን ወሌን ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።

አዲሱ የዛምቢያ አየር መንድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ፣ አውሮፓ እና እስያ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ከሐምሌ 25 ጀምሮ አዲሱን የኃላፊነት ቦታ ተረክበዋል።

የአየር መንገዱን አሠራር እና የደንበኞች አገልግሎት ማሻሻል፣

የበረራ መስመሮችን ማስፋፋት፣

አጋርነቶችን ማጠናከር፣

የፋይናንስ ዘላቂነትን ማረጋገጥ የተጣሉባችው ኃላፊነቶች ናቸው።

በቅርቡ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊዎች ግርማ ዋቄ እና ተወልደ ገብረማሪያም በቅደም ተከትል የኡጋንዳ አየር መንገድ እና የኤር ኢንዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0