ኢትዮጵያ እና ማላዊ በደቡባዊ የስደት መስመር የሰዎች ዝውውር መረቦችን ለመበጣጠስ ተስማሙ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ማላዊ በደቡባዊ የስደት መስመር የሰዎች ዝውውር መረቦችን ለመበጣጠስ ተስማሙ

 

ሁለቱ ሀገራት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም በደቡብ የፍልሰት መስመር ጠንካራ የወንጀል ተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል

 

ስምምነቱን የተፈራረሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ ናቸው።

 

በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ እና ማላዊ፦

 

በሁለቱ ሀገራት የሰዎች ዝውውር መረቦችን ለማፍረስ፣

የጋራ የወንጀል ምርመራ ቡድን ለማቋቋም፣

በሕግ ጉዳዮች ትብብር ለማድረግ፣

ተጠርጣሪዎችንና ፍርደኞችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችሉ የሁለትዮሽ ማዕቀፎች ይፈጥራሉ፡፡

​‎የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ “‎ፍልሰትን በአግባቡ ማስተዳደር ከተቻለ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠንና እና ቀጣናዊ ውህደትን ለማጠናከር ያግዛል። በአንፃሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በዜጎችና በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል” ሲሉ በወቅቱ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0