ሞሮኮ ወደ ሴኡታ ለማቋረጥ ሙከራ ያደረጉ 111 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አዋለች
13:56 16.08.2026 (የተሻሻለ: 14:04 16.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሞሮኮ ወደ ሴኡታ ለማቋረጥ ሙከራ ያደረጉ 111 ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አዋለች
በማህበራዊ ሚዲያ የቀረቡ ጥሪዎችን ተከተሎ በሰሜናዊ ሞሮኮ የባሕር ዳርቻ በሚገኘው ፍኒዴቅ ከተማ እና በአካባቢው ቅዳሜ ዕለት 109 ከሰሃራ በታች የመጡ አፍሪካውያን እና ሁለት የሞሮኮ ዜጎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች ጠቁመዋል።
ጉዳዩን የተመለከቱ ቁልፍ ነጥቦች፡-
◻ ከሐምሌ 23 ሙከራ ወዲህ ስፔን በሴኡታ የባሕር ላይ አጥር የተከለች ሲሆን ከ500 በላይ ተጨማሪ ፖሊሶችን በማሰማራት በሴኡታ የሚገኘውን አጠቃላይ የፖሊስ ኃይል ከ1 ሺህ 600 በላይ አድርሳለች።
◻ እጅግ በጣም ተጋላጭነት ጋር ከተያያዙ ጥቂት አጋጣሚዎች ውጭ ስፔን ሕገ-ወጥ ስደተኞች በሴኡታ እንዲቆዩ፣ ወደ ዋናው የሀገሪቱ ክፍል እንዲንቀሳቀሱ ወይም ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኙ አትፈቅድም።
◻ አምስት ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች አሁንም በሴኡታ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹ በከተማዋ የባሕር ዳርቻ ላይ ተጠልለው ይገኛሉ።
◻ ሞሮኮ ድንበር ለማቋረጥ ጥሪ የሚያቀርቡ የማኅበራዊ የትስስር ገጽ መልዕክቶችን በመከታተል አዘጋጆቹን እና ተሳታፊዎቹን በሕግ እንደምትጠይቅ አስጠንቅቃለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X