የባህር ዳር ስታዲየም ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ጊዜያዊ እውቅና ማግኘቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ሀገር ውስጥ ልታካሂድ ነው
11:23 16.08.2026 (የተሻሻለ: 11:24 16.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የባህር ዳር ስታዲየም ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ጊዜያዊ እውቅና ማግኘቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ሀገር ውስጥ ልታካሂድ ነው
ካፍ ለስታዲየሙ ጊዜያዊ የምድብ 3 ፈቃድ መስጠቱን በትናንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።
ውሳኔው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በሜዳው እንዲያደርግ ያስችለዋል።
ሆኖም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ስታዲየሙ አሁንም ያላጠናቀቃቸው ጉዳዮች እንዳሉ ገልጾ፤ ጨዋታ በሚደረግበት ቀን የስታዲየሙን ዝግጁነት እና የደንቦች አተገባበር ለመከታተል የስታዲየም ተቆጣጣሪ ሊመድብ እንደሚችል አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፤ ሀገሪቱ ካፍ ያስቀመጣቸውን ጥብቅ መስፈርቶች ማሟላት ባለመቻሏ ለዓመታት ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን በስደት ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X