የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ሙሉ በሙሉ ዲሞክራሲያዊ ማድርግ አለብን - የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣን
10:29 16.08.2026 (የተሻሻለ: 10:34 16.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ሙሉ በሙሉ ዲሞክራሲያዊ ማድርግ አለብን - የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣን
"የአፍሪካ ሕዝቦችም ለዓለም የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እንዳላቸው መገንዘብ አለብን" ሲሉ የሕዝብ አገልግሎት ኮሚሽን እና የፖሊስ አማካሪ ፓነል ምክትል ሰብሳቢ ዙኪስዋ ምቆሎምባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው እርምጃ፤ በአሁኑ ወቅት "አምስት ሀገራት ብቻ ድምጽን በድምጽ በመሻር ያለ ምንም ተጠያቂነት የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን የማገድ መብት የሚሰጣቸውን" የተመድ የፀጥታው ምክር ቤትን መለወጥ ነው ብለዋል።
አፍሪካ "በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ እና በባሕልም ያለ ምንም ፍርሃት፣ መገለል ወይም አድሎኦ" በአንድ ድምፅ መናገር አለባት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
"የብዙኃንን ድምፅ የሚያኮስሱ ማናቸውንም አግላይ አሠራሮች፣ ሂደቶች እና ተቋማዊ ልማዶችን ማፍረስ እና ማስወገድ አለብን።"
ፍትሐዊ እና እኩልነት የሰፈነበት ማኅበረሰብ ለመገንባት በአፍሪካውያን ሴቶች ላይ ያልተመጣጠነ ተፅዕኖ ለሚያሳድሩት የዘር፣ የመደብ እና የፆታ "ሥስትዮሽ ጭቆናዎች" መፍትሔ መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ ምቆሎምባ አክለው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X