ኮንጎ ሪፐብሊክ 66ኛውን የነጻነት በዓሏን አከበረች
ኮንጎ ሪፐብሊክ 66ኛውን የነጻነት በዓሏን አከበረች
እ.ኤ.አ. ነሐሴ 15 ቀን 1960 ኮንጎ ከዓመታት የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በኋላ ነጻነቷን አስመልሳለች።
ለዚህ ስኬት መንገድ የጠረጉ ዋና ዋና ሁነቶች፦
🟠 በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ፈረንሳይ የሞግዚትነት ስምምነት በማድረግ ግዛቱን በሁለት ቅኝ ግዛቶች ከፈለች። የቅኝ ግዛቱ ዘመን በከባድ ብዝበዛ፣ በግዳጅ ሥራ እና በከፋ የኑሮ ሁኔታ የተሞላ ነበር፡፡
🟠 የዚህ ዘመን እጅግ አሳዛኝ ከሆኑት ክስተቶች አንዱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኮንጎ ሰዎችን ሕይወት የተቀጠፈው የኮንጎ-ኦሺያን የባቡር መስመር ግንባታ ነው፡፡
🟠በ20ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ላይ የብሔራዊ ነጻነት ንቅናቄዎች በመጠናከራቸው እና በፈረንሳይ ላይ ያለው ዓለም አቀፍ ጫና እየጨመረ በመምጣቱ ከቅኝ ግዛት የመውጣት ሂደት ተጀመረ።
በሶቪዬት ሕብረት እና በኮንጎ ሪፐብሊክ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እ.ኤ.አ መጋቢት 16 ቀን 1964 ተመሠረተ።
በኮንጎ ሪፐብሊክ የሩሲያ ኤምባሲ፣ በብሔራዊ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
አሁን ላይ ኮንጎ በተለይም በኢኮኖሚ፣ በዲጂታል እና በፋይናንስ ዘርፎች "ወደ አዳዲስ ስኬቶች" መጓዟን መቀጠል አለባት ሲሉ ፕሬዝዳንት ዴኒ ሳሱ ንጉዌሶ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X