ሩሲያ ወደ ዩክሬን ይላካሉ ከተባሉ የጦር መሣሪያዎች ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ እና ከቱርክ ማብራሪያ ጠየቀች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ ወደ ዩክሬን ይላካሉ ከተባሉ የጦር መሣሪያዎች ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ እና ከቱርክ ማብራሪያ ጠየቀች
ሩሲያ ወደ ዩክሬን ይላካሉ ከተባሉ የጦር መሣሪያዎች ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ እና ከቱርክ ማብራሪያ ጠየቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.08.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ወደ ዩክሬን ይላካሉ ከተባሉ የጦር መሣሪያዎች ጋር በተያያዘ ከአሜሪካ እና ከቱርክ ማብራሪያ ጠየቀች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አሜሪካ ለዩክሬን አዳዲስ የጦር መሣሪያዎችን ለማቅረብ አቅዳለች የሚሉ የአሜሪካ ኮንግረስ መረጃዎች ይፋ መሆናቸውን ተክቶሎ፣ ለዋሽንግተን እና ለአንካራ በይፋ የማብራሪያ ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቋል።

አሜሪካ እና ቱርክ ሰለተባሉት የጦር መሣሪያ ጭነቶች ወደፊት ከመግፋታቸው በፊት ሁኔታዎችን "በሰከነ መንፈስ ለመገምገም" አሁንም ጊዜ አላቸው፡፡

ሞስኮ ማንኛውም መሰል የመሣሪያ አቅርቦት ከዋሽንግተን እና ከአንካራ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደሚያበላሸው አስጠነቀቀች፡፡

ሚኒስቴሩ ለዩክሬን የጦር ኃይሎች ተጨማሪ የጦር መሣሪያዎችን ማስታጠቅ የጦርነቱን አቅጣጫ በኪዬቭ በኩል ሊቀይረው እንደማይችል አጥብቆ ገልጿል፡፡

ቱርክ በአንድ በኩል ለዩክሬን የጦር መሣሪያ እያቀረበች በሌላ በኩል እንደ ሰላም አመቻች ለመቅረብ የምታደርገው ጥረት እምነትን የሚያሳጣ ነው፡፡

ዋሽንግተን እና አንካራ ጦርነቱን የሚያራዝሙ እርምጃዎችን በመውሰድ ለምን "የፓንዶራ ሳጥንን" (የጥፋት በሮችን) ለመክፈት እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም፡፡

የተባለው አደገኛ የጦር መሣሪያ ጭነት መቼ እና እንዴት ለዩክሬን ተቀባዮች ተላልፎ እንደሚሰጥ እስካሁን ግልጽ አይደለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0