ኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.08.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የስምምነቱን አፈጻጸም የሚከታተል፣ የጋራ እንቅስቃሴዎችን የሚያስተባብር እና ለወደፊት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስትራቴጂካዊ መመሪያ የሚሰጥ “የዮርዳኖስ-ኢትዮጵያ የጋራ የንግድ ምክር ቤት” ይቋቋማል።

የስምምነቱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦

መረጃና አቅም ግንባታ፦ የገበያና ኢንቨስትመንት መረጃዎችን መለዋወጥ፣ የሥልጠናና አቅም ግንባታ ሥራዎችን በጋራ መስራት።

ኢንተርፕራይዞችና ፈጠራ፦ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን፣ አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን እንዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚን መደገፍ።

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፦ በኢ-ኮሜርስ፣ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረት ማድረግ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ አባፊራ አባጆቢር እና የዮርዳኖስ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ኻሊል አል-ሃጅ ተውፊቅ ፈረመውታል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0