ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የዲጂታል ሽግግር ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገባች

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የዲጂታል ሽግግር ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገባች
ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የዲጂታል ሽግግር ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገባች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 15.08.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የዲጂታል ሽግግር ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገባች

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የምርጫ ሳይሆን የግዴታ ጉዳይ መሆኑን በኡጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል የፖሊሲ ጉባኤ ላይ የተናገሩት፤ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ፤ ኢትዮጵያን ለሽግግሩ የምታደርገውን ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ጉባኤው ትኩረት ያደረገባቸው ነጥቦች፦

የሰላምና ደህንነት ትብብር፦ በምስራቅ አፍሪካ የሚስተዋሉ የሰላም ስጋቶችን በጋራና በቅንጅት መመከት፤

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወሳኝነት፦ የቴክኖሎጂ ሽግግር የኅልውና ጉዳይ በመሆኑ በልዩ ትኩረት መሥራት፤

የተጠንቀቅ ኃይሉን ማጠናከር፦ ኃይሉ የቀጣናው ቁልፍ የሰላምና የደኅንነት ተቋም የሚያደርጉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

  ለ5 ቀናት በተካሄደው ጉባኤ፣ የሁሉም አባል ሀገራት ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች እና የመከላከያ ሚኒስትሮችና ተወካዮቻቸው ተሳትፈዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0