የአሜሪካው "ጎልደን ዶም" ፕሮጀክት ሕዋን ወደ ጦር ሜዳነት እየቀየረ ነው - ባለሙያ

የአሜሪካው "ጎልደን ዶም" ፕሮጀክት ሕዋን ወደ ጦር ሜዳነት እየቀየረ ነው - ባለሙያ
ከአሜሪካው "ጎልደን ዶም" ፕሮጀክት ቀጥሎ የሚመጣው ቀጣዩ እርምጃ የአሜሪካ ሚሳኤሎችን እና የጨረር ጦር መሣሪያዎችን ከምድር ከባቢ አየር ውጭ በሕዋ ላይ መሰማራት ሊሆን እንደሚችል የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያው አሌክሴይ ሊዮንኮቭለስፑትኒክ ገልጸዋል።
ይህም በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱት የ"ፓትሪዮት" እና "የታድ" የሁለገብ መከላከያ ሥርዓቶች ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የእንቅስቃሴ ኃይል ተኮር ሚሳኤል መታገጃዎችን እንዲሁም በሕዋ ላይ የተመሠረተ የጨረር (ሌዘር) ፕሮግራምን ያካትታል፤ በዚህ ፕሮግራም ሥር በሕዋ ላይ የምትገኝ ምህዋራዊ መድረክ ባለ 8 ሜጋዋት የሌዘር ኃይል በመጠቀም በብርሃናዊ አስተዋይ መሣሪያዎች እይታ ሥር የሚገባውን ማንኛውንም አካል ማቃጠል እንደምትችል ባለሙያው አብራርተዋል።
"ለዚህ የሳተላይት ስብስብ ዋናው መስፈርት ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ነው። የስታርሊንክ ሳተላይት ስብስብ በሰከንድ ከ200 እስከ 300 ሜጋ ባይት የሚያስተላልፍ ሲሆን ይህም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ሽቦ አልባ ግንኙነት ተደርጎ ይወሰዳል፤ በአሁኑ ወቅት እየተዘረጋ የሚገኘው እና ትራምፕ "ጎልደን ዶም" ብለው የሚጠሩት "የስታርሺልድ" ሳተላይት ስብስብ ግን በሰከንድ እስከ 15 ጊጋቢት በሚደርስ ፍጥነት ይሠራል" ሲሉ ሊዮንኮቭ ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. በ2025 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደራቸው ለአሜሪካ የአየር ክልል ከፍተኛ ደረጃ ያለው ጥበቃ ለመስጠት ያለመ እና 175 ቢሊዮን ዶላር የተመደበለትን የጎልደን ዶም የሚሳኤል መከላከያ ፕሮግራም ማስጀመሩን አስታውቀው ነበር።
ቀደም ሲል የአሜሪካ የሕዋ ኃይል ጄኔራል ማይክል ጌትላይን እንደገለጹት፣ በጎልደን ዶም የሚሳኤል መከላከያ ሥርዓት ግንባታ ላይ የተሳተፉ በርካታ የአሜሪካ ኩባንያዎች የመጀመሪያውን ወሳኝ ፍተሻ በስኬት አጠናቀዋል።
በፍተሻው ላይ ከተሳተፉት ኩባንያዎች መካከል ስፔስ ኤክስ እና ኖርዝሮፕ ግሩማን ይጠቀሳሉ። በመጀመሪያው ምዕራፍ ተቋራጮቹ ከመረጃ መቀበያ ሴንሰሮች ወደ መታገጃ መሣሪያዎች የሚደረገውን የመረጃ ልውውጥ የሞከሩ ሲሆን፣ የማንቀሳቀሻ ሞተር ሥርዓቶችንም ሥራ አሳይተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X