ለግንባታ እና ጥገና 108 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
ለግንባታ እና ጥገና 108 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
አስተዳደሩ የተጠቀሰውን ወጪ በበጀት ዓመቱ 24 ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ለተለያዩ አዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ ደረጃ ማሻሻል እና ጥገና ለማከናወን ማዋሉን አስታውቋል።
የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች፦
580 ኪ.ሜ አዳዲስ እና ፈጣን፣ 105 ኪ.ሜ የኮንክሪት እና 12.7 ኪ.ሜ የፌደራል ዋና መንገዶች ተጠግነዋል፡፡
238 ኪ.ሜ የሚሸፍኑ መንገዶች ደረጃቸው ተሻሽሏል፡፡
የሞጆ-ሐዋሳ ፈጣን መንገድ፣ የባቱ-አርሲ ነገሌ፣ የአምቦ-ወሊሶ እና የአንኮበር መንገዶች ዋናዎቹ ፕሮጀክቶች ውስጥ ናቸው።
ኢትዮጵያ ከዚህ ኢንቨስትመንት ምን ታገኛለች?
በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈሚ ኢትዮጵያ በዴቻ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ የመንገድ መሠረተ ልማቱን አበርክቶዎች አብራርተዋል።
የንግድ እና ገበያ ትስስር ማጠናከር፦ የአርሶ አደሩን የግብርና ምርቶች ወደ ማዕከላዊ ገበያ በፍጥነት ለማድረስ እና የሸቀጦችን ዝውውር በማፋጠን የዋጋ ንረትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
የጉዞ ጊዜ እና ወጪ መቀነስ፦ የፈጣን እና ዋና ዋና መንገዶች ጥገና ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የጉዞ ጊዜን፣ የነዳጅ ብክነትን እና የየብስ ትራንስፖርት ወጪን ይቀንሳል፡፡
ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተዳራሽነት፦ የገጠር እና የከተማ ክፍሎችን በማስተሳሰር ማህበረሰቡ የጤና፣ የትምህርት እና የንግድ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኝ ያመቻቻል።
የከተሞች ትራንስፖርት መሳለጥ፦ አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ምቹ፣ ጽዱ፣ ሰፋፊ እና የትራፊክ ፍሰትን የሚያቀላጥፉ ሆነው ገጽታን ቀይረዋል፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X