አልጄርያ እና ኒጀር የካፍራ ደቡብ-ምሥራቅ 1 የነዳጅ ፍለጋን በመጀመር ወደጅነታቸውን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሸጋገሩ
19:25 14.08.2026 (የተሻሻለ: 19:34 14.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አልጄርያ እና ኒጀር የካፍራ ደቡብ-ምሥራቅ 1 የነዳጅ ፍለጋን በመጀመር ወደጅነታቸውን ወደ ላቀ ምዕራፍ አሸጋገሩ
የአልጄርያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፊ ግሪብ ለሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት የኒጀር ርዕሰ መዲና ኒያሜ ደርሰዋል። ከኒጀር አቻቸው አሊ ማሃማኔ ላሚን ዘይን ጋር በመሆንም የነዳጅ ፍለጋ ቁፋሮው በይፋ አስጀምረዋል።
የነዳጅ ፍለጋው መጀመር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ውስጥ ከፖለቲካዊ መቀራረብ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚና የኃይል ትብብር የሚደረግ ሽግግር እንደሆነም ተገልጿል። የኃይልና የሃይድሮካርበን ዘርፎችም በአዲሱ የትብብር ምዕራፍ ዋና ትኩረት ሆነዋል።
ቀደም ሲል የሚከተሉት ሁለት ቁልፍ ሁነቶች ተካሂደዋል፦
▪ የቅርቡ በኒያሜ የኃይል ማመንጫ ጣብያ ምርቃት፤
▪ የአልጄርያ-ኒጀር ትብብር ከፍተኛ የጋራ ኮሚሽን ሁለተኛ ስብሰባ ውጤቶችም ለትብብሩ አዲስ አቅጣጫን አስቀምጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X