ከቆሻሻ ወደ ሀብት፦ የኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀውስ ወደ ዕድል መቀየር የሚችል ፈተና?

© telegram sputnik_ethiopiaከቆሻሻ ወደ ሀብት፦ የኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀውስ ወደ ዕድል መቀየር የሚችል ፈተና?
ከቆሻሻ ወደ ሀብት፦ የኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀውስ ወደ ዕድል መቀየር የሚችል ፈተና? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 14.08.2026
ሰብስክራይብ

ከቆሻሻ ወደ ሀብት፦ የኢትዮጵያ የፕላስቲክ ቀውስ ወደ ዕድል መቀየር የሚችል ፈተና?

 

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ386 ሺህ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመረታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው በአግባቡ ባለመወገዱ እና ከ10 በመቶ ያነሰው ብቻ እንደገና ጥቅም ላይ በመዋሉ በከተሞች፣ በግብርና እና በውኃ አካላት ላይ ከፍተኛ የአካባቢና የጤና ስጋት ደቅኗል።

 

የችግሩ ገጽታ እና ዋና ዋና አኃዞች፦

ፕላስቲክ ከከተሞች ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ እስከ 11.78% (በአዲስ አበባ እስከ 20%) ድርሻ ይይዛል፡፡

 

በአቃቂና አዋሽ ወንዞች፣ በጣና እና ሐዋሳ ሐይቆች (የሐዋሳ ሀይቅ 60% የባሕር ዳርቻ ቆሻሻ ፕላስቲክ ነው) ላይ ከፍተኛ ብክለት እያስከተለ ይገኛል፡፡

 

የታፈኑ የፍሳሽ ማስወገጃዎች ጎርፍ እንዲፈጠር ያደርጋሉ፤ በግብርና መሬትና በእንስሳት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ለሕዝብ ጤና ስጋት ሆኗል።

 

ከቀውስ ወደ "ክብ" ኢኮኖሚ ሥርዓት ሽግግር

 

🟢 ዘመናዊ የመልሶ ማቀናበሪያዎችን ፋብሪካዎች ኢንቨስትመንት ማበረታታትና ማበራከት፡፡

🟢በየመንገዱ የሚለቅሙትን ሕጋዊ በማድረግ ደህንነታቸውንና ገቢያቸውን ማረጋገጥ)

 

🟢 የከተሞች እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ (በተለይም በሐይቆች እና በወንዝ ዳርቻዎች) ከለላ ማድረግ፡፡

🟢 አምራቾችና አስመጪዎች ፕላስቲኮችን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል የቆሻሻ ማስወገድ ወጪ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0