የእስራኤል አየር ጥቃት በደቡባዊ ሊባኖስ ተፈናቃዮችን የመመለስ ጥረት እያደናቀፈ ነው

ሰብስክራይብ

የእስራኤል አየር ጥቃት በደቡባዊ ሊባኖስ ተፈናቃዮችን የመመለስ ጥረት እያደናቀፈ ነው

በማንሱሪ ከተማም የእስራኤል ጥቃት ሲፈፀም የሚያሳይ ምስል  የወጣ ሲሆን፤ በድንበር አከባቢዎች የመኖርያ ቤቶች ማፍረስን ጨምሮ፣ በእስራኤል ኃይሎች የሚፈፀሙ ጥሰቶች እየቀጠሉ መሆኑን የሊባኖስ ጦር አስታውቋል።

የመኖርያ ቤቶች መፍረስም ከሊባኖስ መንግሥት ጠንካራ ተቃውሞና ቁጣን ሲያስከትል፤ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ሀገራቸው በአከባቢው ያላት ወታደራዊ ቆይታ እንደሚቀጥል በቅርቡ መግለፃቸው ደሞ ውዝግቡን አባብሶታል።

የሊባኖስ ባለሥልጣናት በበኩላቸው እስራኤል የድንበር አከባቢዎችን ከህዝብ ነፃ ለማድረግ የማፍረስ ዘመቻዎችን 'የጋራ ቅጣት' ለመፈፀም እየተጠቀመችባቸው ነው ሲሉ ከሰዋል።

የቤቶች እና የመሠረተ ልማቶች ውድመት የጸጥታ ቁጥጥር ለማስፈን እና ተፈናቃይ ሲቪሎችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የማድረግ አቅሙን እያደናቀፈው መሆኑን የሊባኖስ ጦር በተደጋጋሚ ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0