ኢትዮጵያ በሩሲያው የነባር ሕዝቦች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ የተገለሉ ማኅበረሰቦችን መብት ማረጋገጧን ገለፀች
15:55 14.08.2026 (የተሻሻለ: 16:04 14.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሩሲያው የነባር ሕዝቦች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ የተገለሉ ማኅበረሰቦችን መብት ማረጋገጧን ገለፀች
መንግሥት በሩቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩትን ነባር ማኅበረሰቦችን ጨምሮ የሁሉም ሕዝቦች ዕድገትና ደኅንነት እንዲጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን በሩሲያ ሳይቤሪያ ክራስኖያርስክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የነባር ሕዝቦች ፎረም ላይ የተሳተፉት በሩሲያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በአምባሳደሩ ንግግር የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ ሕገ-መንግሥታዊ መብቶች፦ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት ነባር እና ሕዳጣን ማኅበረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር፣ በሀብት የመጠቀም፣ ባህልና ቋንቋቸውን የማሳደግ እንዲሁም በሁሉም የፖለቲካና አስተዳደር እርከኖች የመሳተፍ መብታቸው ተረጋግጧል፡፡
▪ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውህደት፦ ቀደም ሲል ትኩረት አጥተው የነበሩ ማኅበረሰቦች ድምፃቸው እንዲሰማ እና በሀገሪቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ በርካታ ሀገራዊ አሰራሮች ተተግብረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X