የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን የወደብ መሠረተ ልማቶች እና መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ቀጥለዋል - የመከላከያ ሚኒስቴር
15:25 14.08.2026 (የተሻሻለ: 15:34 14.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን የወደብ መሠረተ ልማቶች እና መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ቀጥለዋል - የመከላከያ ሚኒስቴር
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ያወጣቸው ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች፦
በነሐሴ 7 ምሽት፣ በኒኮላዬቭ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በጥቁር ባህር ውስጥ በሚገኙ ሁለት ተሳቢ መርከቦች ላይ የጥቃት ድሮኖች ጥቃት ፈጽመዋል። መርከቦቹ የምዕራባውያን ጦር መሣሪያዎችን ወደ ዩክሬን ወደቦች የሚያጓጉዙ የጭነት መርከቦችን በማጀብ ላይ ነበሩ፤
ነሐሴ 8 ለሊቱን፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና ነዳጅን ለመጫን፣ ለማከማቸት እና ለማጓጓዝ የሚያገለግለው የኢዝማኢል ወደብ የባቡር ጣቢያ በድሮን ጥቃት ተመቷል፤
ከነሐሴ 7 እስከ 8 በነበረው ሌሊት፣ የሩሲያ የአየር መከላከያ ኃይሎች በሩሲያ ክልሎች ላይ የተቃጡ 553 የዩክሬን የቋሚ ክንፍ ዓይነት ድሮኖችን አየር ላይ አክሽፈው ደምስሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X