ናሚቢያ ለኩባ ያላትን ድጋፍ ዳግም አረጋገጠች፤ የፊደል ካስትሮን ሥራዎች ዘክራለች - የናሚቢያ ፕሬዝዳንት

ሰብስክራይብ

ናሚቢያ ለኩባ ያላትን ድጋፍ ዳግም አረጋገጠች፤ የፊደል ካስትሮን ሥራዎች ዘክራለች - የናሚቢያ ፕሬዝዳንት

"የፕሬዝዳንት ፊደል ካስትሮን መቶኛ የትውልድ ቀን ናሚቢያ ማክበሯ ለትዝታ ብቻ ሳይሆን፣ ለሁለቱ ሕዝቦቻችን አንድነት መሰረት ለሆኑት እሴቶች በምስጋና፣ በአጋርነት እና በታደሰ ቁርጠኝነት ነው" ሲሉ ፕሬዝዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋ የቀድሞ የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ የልደት ቀን በዊንድሆክ በተዘጋጅ ሥነ-ሥርዓት በተከበረበት ወቅት ተናግረዋል፡፡



በካስትሮ አመራር ወቅት የናሚቢያ የነፃነት ታሪክ ከኩባ ድጋፍ ጋር በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን በማስታወስም፣ የኩባ ሕዝብ ናሚቢያ ለነፃነቷ ባደረገችው ትግል ቁርጠኛ አጋር ሆኖ እንደቆየ ገልፀዋል።

"ስለሆነም ፕሬዝዳንት ፊደል ካርትሮን የኩባ አብዮት መሪ ብቻ ሳይሆኑ፣ የአፍሪካ ወዳጅ በመሆናቸው በጥልቅ ክብርና ምስጋና እናስታውሳቸዋለን" ሲሉም አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0