ታሪካዊ ስኬት፦ አንድ ኪሎግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2,275 ዶላር ተሸጠ
08:04 13.08.2026 (የተሻሻለ: 08:14 13.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታሪካዊ ስኬት፦ አንድ ኪሎግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2,275 ዶላር ተሸጠ
በሻንጋይ በተካሄደው የ"ሶለም ሶርሲንግ ሻንጋይ ኩዌይ" ዓለም አቀፍ የቡና ጨረታ ላይ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአንድ ኪሎግራም 2,275 የአሜሪካ ዶላር (364,000 ብር ገደማ) በመሸጥ አዲስ የዓለም ክበረ-ወሰን አስመዝግቧል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
ቡናው በሲዳማ ክልል በንሳ አካባቢ በአርሶ አደሮች ተመርቶ በዘመናዊ የ"አናኤሮቢክ" ማቀናበሪያ ዘዴ የተዘጋጀ ነው።
የቡናው ተፈጥሮአዊ ጣዕም፣ ልዩ መዓዛ እና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ የዓለም አቀፍ ገዢዎችን ቀልብ ስቧል።
ይህ ስኬት የኢትዮጵያ ቡና በጥራትና በእሴት ጭመራ በዓለም ገበያ ያለውን የበላይነት የሚያረጋግጥና ለአምራች አርሶ አደሮች ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ እንደሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡና ማኅበር ገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X