የኢትዮጵያ አዲስ የቡና ልማት ፓኬጅ፦ በሄክታር 21 ኩንታል የማምረት ግብ
15:15 12.08.2026 (የተሻሻለ: 15:24 12.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አዲስ የቡና ልማት ፓኬጅ፦ በሄክታር 21 ኩንታል የማምረት ግብ
ኢትዮጵያ የቡና ምርታማነትን በአሁኑ ወቅት ካለው በሄክታር አማካይ 9 ኩንታል ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ አዲስ ሀገራዊ የቡና ልማት ፓኬጅ ይፋ አድርጋለች።
ኢትዮጵያ በዚህ ፓኬጅ ምን ታሳካለች?
🟠 በ1.15 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ዘመናዊ የአመራረት ሥርዓት ለመዘርጋት ያስችላታል፡፡
🟠 ምርታማነትን በሄክታር ከ130% በላይ ያሳድጋል፡፡
🟠 የቡና ወጪ ንግድ ዓመታዊ ገቢ ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ የያዘችውን ግብ ያፋጥናል።
🟠 ተጨማሪ መሬት ሳያስፈልግ የነባር ማሳዎችን ምርታማነት ይጨምራል፡፡
🟠 እንደ ብራዚል እና ቬትናም ካሉ የዘርፉ ግዙፍ አምራች ሀገራት ጋር ያለውን የውጤታማነት ልዩነት ያጠብባል።
🟠 ከ6 ሚሊዮን በላይ የቡና አምራች አርሶ አደሮችን ገቢና የኑሮ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሽላል።
አዲሱ አሰራር ምርጥ ዘር መጠቀምን፣ የተቀናጀ የአፈርና መስኖ አጠቃቀምን፣ የቡና ጥግግትና ግረዛን፣ ተገቢ ጥላና የተባይ መከላከልን እንዲሁም የተሻሻለ የምርት አሰባሰብና የዛፎች ዕድሳትን ያካተተ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X