የሊቢያ የድፍድፍ ነዳጅ ወጭ ንግድ ገቢ በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ከታቀደው 9% ብልጫ በማሳየት ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኖ ተመዘገበ

ሰብስክራይብ

የሊቢያ የድፍድፍ ነዳጅ ወጭ ንግድ ገቢ በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ከታቀደው 9% ብልጫ በማሳየት ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኖ ተመዘገበ

የሀገሪቱ የኢኮኖሚና ንግድ ሚኒስቴር ማክሰኞ ዕለት ባወጣው መረጃ መሠረት፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ወደ 246 ሚሊዮን ባሬል ገደማ ድፍድፍ ነዳጅ የተመረተ ሲሆን፣ ይህም ከታቀደው 252 ሚሊዮን በርሜል ጋር ሲነጻጸር በጥቂቱ ያነሰ ቢሆንም የገቢ መጠኑ ግን ከዕቅዱ በላይ ማደግ ችሏል።

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው፤ ይህ የግማሽ ዓመት ውጤት በሊቢያ ሁለቱ ሕግ አውጪ አካላት መካከል በሚያዝያ የተፈረመውን የጋራ የፋይናንስ ወጪ ስምምነት በተግባር ለማዋል 'በጎ ማሳያ' ነው። ይህም ባለፉት 13 ዓመታት ውስጥ በሀገሪቱ የጋራ ወጪ ላይ መግባባት ሲደረስ የመጀመሪያው ነው።

በሚኒስቴሩ መግለጫ መሠረት በቀጣዩ ምዕራፍ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ትኩረት ይደረግባቸዋል፦

▪ በመንግሥት ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ ማስቀጠል፤

▪ አፈጻጸምን ከእውነተኛው የገቢ መጠን ጋር ማገናኘት፤

▪ ሀብትን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከርና የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ማዋል፤

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0