አሜሪካ ባለፈው ዓመት ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ለተገደሉት የየመን ንጹሐን ዜጎች ኃላፊነት ወሰደች
11:35 12.08.2026 (የተሻሻለ: 11:44 12.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አሜሪካ ባለፈው ዓመት ባካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ለተገደሉት የየመን ንጹሐን ዜጎች ኃላፊነት ወሰደች
ባለፈው ዓመት አሜሪካ በየመን በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ ባካሄደችው የአየር ድብደባ በጥቅሉ 153 ንጹሐን ዜጎች ሲገደሉ ተጨማሪ 250 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የፔንታጎን ግምገማ አመላክቷል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህልፈት እና ለጉዳት ለዳረጉ ሦስት ጥቃቶች ኃላፊነት መውሰዷ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ተጠያቂነቱን ሲያምን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ ተጨማሪ 15 አጋጣሚዎች አሁንም በግምገማ ላይ ይገኛሉ።
ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀይ ባሕር የመርከብ መስመሮች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ተከትሎ በሁቲዎች ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸው ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X