ናሚቢያ አሜሪካ ለ66 ዓመታት ኩባ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ "የተዳፈነ የዘር ማጥፋት" ስትል ኮነነች
08:00 12.08.2026 (የተሻሻለ: 08:04 12.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ናሚቢያ አሜሪካ ለ66 ዓመታት ኩባ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ "የተዳፈነ የዘር ማጥፋት" ስትል ኮነነች
የቀድሞውን የኩባ መሪ ልደት በማሰብ በሃቫና በተካሄደው የመጀመሪያው የፊደል ካስትሮ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የናሚቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤላጃ ንጉራሬ፤ የአሜሪካ የኩባ ከበባ ደሴቲቱን አስገድዶ ለማንበርከክ የተቀየሰ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ነው ብለዋል።
ማዕቀቡ የኩባን የምግብ፣ የውኃ እና የጤና አጠባበቅ ሥርዓቶች በማሽመድመድ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ትራንስፖርት እንዲስተጓጎል እና ቆሻሻ እንዳይነሳ ማድረጉን ተመድ ገልጿል።
"የኩባ ወንድም እና እህቶቻችን ሆን ተብሎ ተዳፍነው እንዲሞቱ እየተደረገ ነው" ሲሉ ንጉራሬ ተናግርዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሜሪካ ማዕቀቡን እንድታነሳና "የጋራ ቅጣቱን" እንድታቆም እንዲያስገድድ በመጠየቅ፤ ናሚቢያ ከኩባ ጎን ያላትን አብሮነት አረጋግጠዋል።
ቪዲዮው በናሚቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ንጉራሬ እና በኩባ ፕሬዚዳንት በርሙዴዝ መካከል ሰኞ ዕለት የተደረገውን ውይይት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X