ሩሲያ እና ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያውን የበይነ መንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ በሚቀጥለው ወር ሊያካሂዱ ነው
12:35 11.08.2026 (የተሻሻለ: 12:44 11.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ቡርኪና ፋሶ የመጀመሪያውን የበይነ መንግሥታት ኮሚሽን ስብሰባ በሚቀጥለው ወር ሊያካሂዱ ነው
የሩሲያ ባለሥልጣናት እና የኩባንያ ተወካዮች በንግድ፣ ኢኮኖሚ እና ቴክኒክ ትብብር ዙሪያ የሚደረገውን የመጀመሪያ የሁለትዮሽ ኮሚሽን ስብሰባ አጀንዳ ለማጠናቀቅ የዝግጅት ስብሰባ ማካሄዳቸውን የሩሲያ የኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የስብስባው ዋና ዋና ነጥቦች፦
የኢነርጂ ሚኒስትሩ ሴርጌ ሺቪሌቭ የኮሚሽኑ የሩሲያ ወገን ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ሲሆን የመጀመሪያው ስብሰባ መስከረም 6 በሞስኮ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዟል።
ውይይቶቹ የኢነርጂ መሠረተ ልማት፣ የኢንዱስትሪ ትብብር፣ የግብርና ማሽነሪዎች፣ የሲቪል ድሮኖች እና የመድኃኒት ምርቶች እንዲሁም ግብርና፣ ትምህርት እና የእንስሳት ሕክምናን ያካትታሉ።
ሞስኮ የቡርኪና ፋሶን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለማዘመን የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ዝግጁነቷን ገልጻለች።
በተጨማሪም የደቡብ ፌደራል ዩኒቨርሲቲ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የሩሲያ ቋንቋ መምህራንን ወደ ሀገሪቱ ለመላክ አቅዷል።
የፕሬዚዳንት ፑቲን እና ኢብራሂም ትራኦሬን የሐምሌ 29፣ 2023 ግንኙነት የሚያሳይ የማኅደር ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X