አዲስ አበባ የድምጽ ብክለት በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ልትጥል ነው
12:00 11.08.2026 (የተሻሻለ: 12:04 11.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ የድምጽ ብክለት በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት ልትጥል ነው
አዲሱ መመሪያ የበለጠ አስተማሪ እና አጥፊዎችን ቆንጠጥ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ለድምጽ ብክለት የሚጣለው ቅጣት ትንሹ 5 ሺህ ብር፤ ትልቁ ደግሞ 25 ሺህ ብር ነው፡፡
በ2018 በጀት ዓመት 12,376 አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የድምጽ ብክለት ቁጥጥር ተደርጓል፦
▪ 3,116 አገልግሎት ሰጪዎች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፣
▪ 28 ታሽገዋል፣
▪ ከተላለፈ የገንዘብ ቅጣት 140,000 ብር ተሰብስቧል፡፡
የቅጣት እርከኑን በአዲስ አበባ ለመተግበር የሚያስችለው አዲስ ረቂቅ መመሪያ ለከተማ አስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ መላኩን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X