አሜሪካ ለዩክሬን በምታደርገው ድጋፍ እስከ 2030 ድረስ ያለ ጃቭሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል እንደማይኖራት ተገለጸ

© telegram sputnik_ethiopiaአሜሪካ ለዩክሬን በምታደርገው ድጋፍ እስከ 2030 ድረስ ያለ ጃቭሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል እንደማይኖራት ተገለጸ
አሜሪካ ለዩክሬን በምታደርገው ድጋፍ እስከ 2030 ድረስ ያለ ጃቭሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል እንደማይኖራት ተገለጸ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.08.2026
ሰብስክራይብ

አሜሪካ ለዩክሬን በምታደርገው ድጋፍ እስከ 2030 ድረስ ያለ ጃቭሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤል እንደማይኖራት ተገለጸ

​ እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2024 የተደረገው ተጨማሪ ትዕዛዝ ከአምራቾች የማምረት አቅም በላይ በመሆኑ፤ አሜሪካ የጃቭሊን የፀረ-ታንክ ሚሳኤል ክምችቷን ቢያንስ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ መመለስ እንደማትችል የፔንታጎን የበጀት ሰነዶች ይፋ አድርገዋል።

​እ.ኤ.አ ከ2022 እስከ 2025 ባሉት ዓመታት የአሜሪካ ጦር ክምችቱን ለመተካት 9 ሺህ 374 ሚሳኤሎችን የገዛ ቢሆንም ርክክቦች የሚጀምሩት ውሉ ከተፈረመ ከበርካታ ዓመታት በኋላ ነው።

​በ2024 በጀት የወጣለት የመጨረሻው ዙር የ944 ሚሳኤሎች ግዢ የሚጀምረው በነሐሴ 2030 ሲሆን ርክክቡም በበርካታ ዓመታት ተከፋፍሎ የሚከናወን ይሆናል።

​የአንድ ጃቭሊን ሚሳኤል ሙሉ ግዢ እና የማምረት ሂደት እስከ 4.5 ዓመታት፤ የተወንጫፊ መቆጣጠሪያው ደግሞ ከ4 ዓመታት በላይ የሚወስድ በመሆኑ በፍጥነት መተካቱን የማይቻል ያደርገዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0