ኢራን አማራጭ እይታዎችን በማቅረብ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እና ስፑትኒክን አደነቀች

ሰብስክራይብ

ኢራን አማራጭ እይታዎችን በማቅረብ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን እና ስፑትኒክን አደነቀች

 

"​የኢኮኖሚ ተሳታፊዎች ትክክለኛ እና ከጊዜው ጋር የሚሄድ ውሳኔ ማሳለፍ እንዲችሉ ወቅታዊ፣ ግልጽ መረጃ እና የተለያዩ ምንጮች ያስፈልጓቸዋል" ሲሉ የኢራን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀሚድ ጋንባሪ ለስፑትኒክ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

​ጋንባሪ አክለውም ከተለመዱት መደበኛ ትርክቶች ባሻገር አማራጭ እይታዎችን የሚያቀርቡ መገናኛ ብዙኃን፤ መንግሥታትም ሆኑ የግሉ ዘርፍ ተዓማኒ እና ትክክለኛ የኢኮኖሚ ውሳኔ እንዲሰጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለዋል።

 

​“ይህም መንግሥታት የበለጠ ምክንያታዊ እና ተጨባጭ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ የሚረዳ ሲሆን ፖሊሲዎችም የሀገራትን ጥቅም ባስከበረ መልኩ እንዲቀረጹ ያስችላል።”

​በዚህ በኩል ስፑትኒክን ጨምሮ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተጨማሪ ድምፆችን እና እይታዎችን በማቅረብ ረገድ አዎንታዊ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0