ማዳጋስካር የግል ኩባንያዎችን የበላይነት ያስቀራል የተባለውን የመጀመሪያውን የመንግሥት የነዳጅ ጭነት ልትረከብ ነው

ሰብስክራይብ

ማዳጋስካር የግል ኩባንያዎችን የበላይነት ያስቀራል የተባለውን የመጀመሪያውን የመንግሥት የነዳጅ ጭነት ልትረከብ ነው

​ማዳጋስካር በዚህ ሳምንት የመጀመሪያውን የናፍጣ ነዳጅ ጭነት በቀጥታ ከቻይና እንደምትረከብ የሀገሪቱ የኃይል ሚኒስትር ራዶኒሪና ሉካስ ራቤአሪማንጋ መናገራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ጭነቱ ቶታል ኢነርጂስን ጨምሮ በግል ኩባንያዎች ተይዞ የቆየውን የ25 ዓመታት የነዳጅ ሞኖፖሊ የሚያስቀር ነው። በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደረው 'ጂራማ' የተሰኘው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋም በበሚመጡት ወራት የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ አቅዷል።

​ሌሎች የነዳጅ ምርቶችን የጫነ ሁለተኛ መርከብ በዚሁ ሳምንት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በሩቢስ ኢነርጂ ባለቤትነት በሚተዳደረው 'ጋላና' ፋብሪካ የነዳጅ ክምችትና ስርጭት ለማከናወን ውይይቶች ቀጥለዋል።

​ እርምጃው የማዳጋስካር ከፍተኛ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሃምሌ 27 ቀን ያጸደቀውን ሕግ ተከተሎ የመጣ ነው። ሕጉ መንግሥት የነዳጅ ምርቶችን በቀጥታ እንዲያስገባ በመፍቀድ የግል ኩባንያዎች ደግሞ ማከማቸትና ማሰራጨት ላይ እንዲወሰኑ አድርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0