- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የኮንፈረንስ ቱሪዝም፡ አፍሪካ በዓለም 3.1 ትሪሊዮን ዶላር ከሚያመነጨው ዘርፍ እንዴት ትጠቀም?

የኮንፈረንስ ቱሪዝም፡ አፍሪካ ከ3.1 ትሪሊዮን ዶላር ዘርፍ እንዴት ትጠቀም?
ሰብስክራይብ

"የኮንፈረንስ ወይም MICE ቱሪዝም በመባል የሚታወቀው ዘርፍ በ180 ሀገራት ውስጥ በተደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች ወደ 1.6 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አዘዋውሯል፤ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ገቢም አስገኝቷል። ስለዚህ በቢሊዮኖች ሳይሆን በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ገቢ ነው የሚገኝበት። ይህም በቀጥታ ሽያጭ ብቻ የሚገኝ ነው። ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ሲጨምር ወደ 3.1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ይደርሳል። ይህም በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ሲሰላ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። በእርግጥ ይህ ኢንዱስትሪ ራሱ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል።" ሲሉ ዮአዳን ጥላሁን፣ የ"ፍሎውለስ ኢቨንትስ" መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዝግጅቶችና ኤግዚቢሽን አዘጋጆች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ የዝግጅቶችና ስብሰባዎች ኢንዱስትሪ ለዓለምና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ያለውን ግዙፍ ፋይዳ፣ እንዲሁም ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ያለውን ስትራቴጂያዊ ሚና እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ከኢኮኖሚ ትስስርና ከአህጉራዊ ትብብር አንፃር የአፍሪካ ወደብ አልባ ሀገራት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችና ዕድሎች ከፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)ጋር እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0