የምግብ ሉዓላዊነት ቅድሚያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው - ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ
12:04 10.08.2026 (የተሻሻለ: 12:14 10.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የምግብ ሉዓላዊነት ቅድሚያ የሚሰጠው የኢትዮጵያ አጀንዳ ነው - ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት እንዳቀደ ከሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውቀዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማሻሻያ ይደረግባቸዋል ተብለው የተጠቀሱ ቁልፍ ዘርፎች፦
ቴክኖሎጂ፦ የዲጂታል አሠራርን በማስፋፋት አገልግሎቶችን ቀልጣፋ እና ተደራሽ ማድረግ፣
የሕዝብ አገልግሎት፦ ሙስናና ስርቆትን በማስቀረት ሕዝቡን ማገልገል፣
ኢነርጂ፦ ለኒውክሌር ኃይል ማመንጫ መሠረት መጣል እና የተፈጥሮ ጋዝን ለኢንዱስትሪና ለተሽከርካሪዎች ማዋል፣
ግብርና፦ ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት፣ የመስኖ እና ክላስተር እርሻዎችን በማስፋፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣
የከተማ ልማት፦ የኮሪደር ልማትን ወደ ክልሎች በማስፋፋት የመሠረተ ልማት፣ የቤት እና የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል።
“በሚቀጥሉት ዓመታት ውስጥ በምግብ እራስን መቻል ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይቀጥላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የምግብ ዋስትና መረጋገጡ በክልል ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X