የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ1945ቱ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የአሜሪካን ሚና በተመለከተ ጃፓን ዝምታ መምረጧን ኮነኑ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ1945ቱ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የአሜሪካን ሚና በተመለከተ ጃፓን ዝምታ መምረጧን ኮነኑ
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ1945ቱ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የአሜሪካን ሚና በተመለከተ ጃፓን ዝምታ መምረጧን ኮነኑ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.08.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በ1945ቱ የአቶሚክ ቦምብ ጥቃት የአሜሪካን ሚና በተመለከተ ጃፓን ዝምታ መምረጧን ኮነኑ

​“የወቅቱ የጃፓን አመራር በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ የወደቁት የአቶሚክ ዩኦፎዎች ናቸው ብሎ ያምናል?” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጽፈዋል።

​በሌላ በኩል [ከተማዋ ላይ የወደቀውን] ቦምብ የጣለው ‘የአሜሪካ ጦር አውሮፕላን’ እንደሆነ በግልጽ ለመናገር “ድፍረት በማሳየታቸው” ለናጋሳኪ ከንቲባ ሺሮ ሱዙኪ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

​ቀደም ሲል የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ አሜሪካ እ.ኤ.አ ነሐሴ 1945 በሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶሚክ ቦምቦችን መጣሏን በተመለከተ ዝምታን የመረጡ ሲሆን የሂሮሺማ ከንቲባ ካዙሚ ማትሱይም ይህንኑ አቋም ተከትለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0