የቅኝ ግዛት ድንበር የእኩልነት እጦት ምልክት እና የሞት ወጥመድ ሆኗል - ሞሮኳዊው ባለሙያ ስለ ሴኡታ ቀውስ መንስኤ

ሰብስክራይብ

የቅኝ ግዛት ድንበር የእኩልነት እጦት ምልክት እና የሞት ወጥመድ ሆኗል - ሞሮኳዊው ባለሙያ ስለ ሴኡታ ቀውስ መንስኤ

የስደተኞች ቀውስ ሊከሰት የቻለው "የካፒታል ፍሰት በነጻነት እንዲንቀሳቀስ ፈቅዶ፤ የሰዎች ነጻ እንቅስቃሴን በሚከለክለው" ሥርዓት ጥልቅ መዋቅራዊ መንስኤዎች የተነሳ እንደሆነ ሳይድ ባካሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል።

የውጥረቱ ዋና ዋና ስረ መንስኤዎች፦

የሴኡታ እና መሊላ በቅኝ ግዛት መያዝ፦ በአፍሪካ ምድር  "በአጥር፣ የክትትል ሥርዓቶች እና በትጥቅ ጥበቃዎች" የተከለለ ድንበር ፈጥሯል።

የኢኮኖሚ ኢ-እኩልነት እና ተስፋ አስቆራጭ ማኅበራዊ ሁኔታ፦ ከፍተኛ የሥራ አጥነት፣ ከትምህርት መገለል እና ወጣቶችን እንደ "ተረፈ ሕዝብ" የሚቆጥረው የኒዮሊበራል አካሄድ፤ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ከሚታየው "የአውሮፓ ብልጽግና" ጋር ሲነጻጸር ከባድ ተስፋ መቁረጥን ፈጥሯል።

ዲጂታል መር አሳሳች መረጃዎች፦ ድንበሩ "በሕግ ተከፍቷል" የሚሉ የሐሰት መረጃዎች በሕገ-ወጥ የሰው አስተላላፊዎች መረቦች ግነት በማኅበራዊ ሚዲያ በፍጥነት ተሰራጭተዋል።

የካፒታሊዝም ተቃርኖዎች፦ ካፒታልና ቁሳቁሶች በሜዲተራኔያን ባሕር በነጻነት ሲዘዋወሩ፤ ሠራተኞችና ደሃ ወጣቶች ግን በግንቦችና በቪዛ ይከለከላሉ።

 

"ወታደራዊ ድንበሮች የሚጠብቁት ሠራተኞችን ወይም ሕዝቦችን ሳይሆን፤ እኩልነት አልባውን ዓለም አቀፍ ሥርዓት እና በዘመናት የቅኝ አገዛዝ ብዝበዛ የተፈጠሩ ጥቅሞችን ነው" ሲሉ ባካሊ አፅንኦት ተሰጥተዋል።

 

ቪዲዮው የሴኡታን ድንበር ለማጠናከር በታራጃል ወደብ ላይ የ500 ሜትር የአየር ግፊት አጥር እና የባሕር ላይ ተንሳፋፊ ምልክቶች ሲቆሙ ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0