ሞሮኮ የሴኡታን ቀውስ አልጠነሰሰችም - የሞሮኮ ፖለቲካ ቢሮ አባል

© telegram sputnik_ethiopiaሞሮኮ የሴኡታን ቀውስ አልጠነሰሰችም - የሞሮኮ ፖለቲካ ቢሮ አባል
ሞሮኮ የሴኡታን ቀውስ አልጠነሰሰችም - የሞሮኮ ፖለቲካ ቢሮ አባል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.08.2026
ሰብስክራይብ

ሞሮኮ የሴኡታን ቀውስ አልጠነሰሰችም - የሞሮኮ ፖለቲካ ቢሮ አባል

 

መሬት ላይ ያሉ እውነታዎች ሞሮኮ ቀውሱን እንዳላቀደች ወይም እንዳላደራጀች ያሳያሉ ሲሉ ሰኢድ ባካሊ በክስተቱ ዙሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሞሮኮ እጇ አለበት የሚለውን ሴራ ፉርሽ የሚያደርጉ ዋና ዋና ነጥቦች፦

የደህንነት መረጃ ማስረጃ የለም፦ የስፔን የደህንነት መሥሪያ ቤት በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረቦች እና በሞሮኮ መንግሥት መካከል ምንም አይነት ግንኙነት አላገኘም።

የስፔን እና የሞሮኮን ወቅታዊ ግንኙነት ይቃረናል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንቼዝ ከሞሮኮ ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመፍጠር ከፍተኛ ትኩረት የሰጡ ሲሆን ግንኙነቱንም "በቅርብ አስርት ዓመታት ውስጥ የተሻለው ነው"  ሲሉ ገልጸዋል።

የተከሰተበት ጊዜ አያሳምንም፦ ቀውሱ የተቀሰቀሰው ንጉሱ እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሞሮኮን የዘውድ ቀን ለማክበር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተሰበሰቡበት ወቅት መሆኑ፤ መንግሥት "በዚያ ክልል እና በዚያ ቅጽበት ለመቆጣጠር አዳጋች እና ሞት ሊያስከትል የሚችል ቀውስ ይፈጥራል" ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚጠበቅ አይደለም።

የስፔን ባለሥልጣናት ለሞሮኮ ትብብር እውቅና ሰጥተዋል፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳንቼዝ እና የስፔን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የሞሮኮን "አርዓያዊ ትብብር" እና ሁኔታውን ለመቆጣጠር ያደረገችውን ወሳኝ ጥረት አወድሰዋል።

"ቀውሱ በተከሰተበት ወቅትም ቢሆን ሳንቼዝ ሞሮኮ ናት ያቀነባበረችው ብሎ ከመወንጀል ተቆጥበዋል። ይልቁንም ሞሮኮን እንደ አጋር አድርገው ነው የጠቀሷት" ሲሉ ባካሊ አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0