የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
19:23 08.08.2026 (የተሻሻለ: 19:24 08.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ነው - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ፤ በቅርቡ የፀደቀውን “የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018” አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ “አዋጁ አጠቃላይ የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ደህንነት ለማረጋገጥና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የተወሰደ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው” ብለዋል።
በአዋጁ ከተለዩ 12 ቁልፍ የመሠረተ ልማት ዘርፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
▪ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ኮሙኒኬሽን፣
▪ ፋይናንስ፣
▪ ፀጥታና ደህንነት፣
▪ ትራንስፖርት፣
▪ትምህርት፣
▪ ጤና፣
▪ ውሃና ኢነርጂ።
አዋጁ የቁልፍ መሠረተ ልማት ባለቤቶች ሊወጧቸው የሚገቡ 18 ዋና ዋና የሳይበር ደህንነት ግዴታዎችንም በዝርዝር አስቀምጧል፦
ብቁ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን ማሰማራት፣
የአቅርቦት ሰንሰለት ደህንነትን ማረጋገጥ፣
የክትትልና ምላሽ ማዕከል ማደራጀት፣
የሳይበር ክስተት ሲያጋጥም በ48 ሰዓታት ማሳወቅ።
አዋጁ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ተቋማት ራሳቸውን እንዲያደራጁ የአንድ ዓመት የቅድመ ዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X