ኢትዮጵያ የቻይናዋ ሻንዶንግ ግዛት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በስፋት እንዲሰማሩ ጥሪ አቀረበች
17:53 08.08.2026 (የተሻሻለ: 17:54 08.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የቻይናዋ ሻንዶንግ ግዛት ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በስፋት እንዲሰማሩ ጥሪ አቀረበች
ቤጂንግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ በቻይና ሻንዶንግ ግዛት ጂናን፣ ዌይፋንግ እና ዪንታይ ከተሞች በተካሄደው የ2026 የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት የጉብኝት መርኃ-ግብር ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጉን አስታውቋል።
ኤምባሲው በዝግጀቱ ላይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የቱሪዝም አቅም እና ባሕላዊ ቅርሶች አስተዋውቋል።
መድረኩ በኢትዮጵያ እና በሻንዶንግ ግዛት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X