የዚምቧቤ ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ጫናዎች አንጻር ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል - ሪፖርት
15:14 08.08.2026 (የተሻሻለ: 15:24 08.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዚምቧቤ ኢኮኖሚ ከዓለም አቀፍ ጫናዎች አንጻር ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል - ሪፖርት
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ባጸደቀው የሀገሪቱ የባለሙያዎች ክትትል ፕሮግራም የመጀመሪያ ግምገማ መሰረት፤ የዚምቧቤ ኢኮኖሚ መረጋጋት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በ2026 የ5% እንዲሁም በዓመቱ አጋማሽ ደግሞ የ4.2% ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል።
ከሰነዱ የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ዕድገቱ በማዕድን ዘርፉ፣ በወርቅ ዋጋ መጨመር እና በግብርናው ዘርፍ ጠንካራ ማገገም የተደገፈ ነው፣
የኃይል ዋጋ ቢጨምርም የዋጋ ግሽበት ዝቅተኛ ሆኖ ቀጥሏል፣
የውጭ ምንዛሪ ገበያው ተረጋግቶ ቀጥሏል፣
የሒሳብ ሚዛን ትርፍ በ2025 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 3.6% የደረሰ ሲሆን ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በ58% እንዲሁም ገቢ ምርቶች በ30% በማደግ አዎንታዊ ሁኔታው በ2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትም ቀጥሏል።
"ይህም የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደርን ለማጠናከር፣ የመጠባበቂያ አቅሞችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም ውዝፍ ዕዳዎችን ማፅዳት እና መክፈሉን ለማስቀጠል ጥሩ ዕድል ይሰጣል" ሲል ሪፖርቱ ጠቁሟል።
ሆኖም ለዋና ዋና ማህበራዊ ፕሮግራሞች ማለትም — ለመሠረታዊ ትምህርት ድጋፍ፣ ለግብርና ፕሮግራም እና ለማኅበራዊ ጥበቃ ስርዓት — የተያዙ የበጀት አጠቃቀም ኢላማዎች በአፈፃፀም ማነስ ምክንያት ሳይሳኩ ቀርተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X