በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የሚተገበር ድንበር ተሻጋሪ የሕብረተሰብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ ስምምነት ሊፀድቅ ነው

ሰብስክራይብ

በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የሚተገበር ድንበር ተሻጋሪ የሕብረተሰብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ ስምምነት ሊፀድቅ ነው

 

ድንበር ተሻጋሪ የሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ዝግጁነት፣ ቅኝት እና ምላሽ አሰጣጥን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድን ለማጠናቀቅ የቀጣናው የጤና አመራሮች በአዲስ አበባ እየመከሩ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

 

መድረኩ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ኢጋድ፣ የዓለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ተወካዮችን አሰባስቧል፡፡

 

እንደ ኮሌራ እና ኤምፖክስ ያሉ በሽታዎች በፍጥነት ድንበር ተሻግረው አጎራባች ሀገራትን የሚያጠቁ በመሆናቸው ቀጣናዊ ትብብር እና የእውነተኛ ጊዜ የመረጃ ልውውጥ ወሳኝ መሆኑ ተነስቷል።

 

በሀገራት መካከል ድንበር ተሻጋሪ የጤና ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተቀናጀ ሕጋዊ አሰራር የሚፈጥር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ይዘጋጃል።

 

በድንበር እና የመግቢያ በሮች አካባቢዎች ጠንካራ የክትትል፣ የመረጃ ልውውጥ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን በጋራ ለመገንባት መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0