ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ የዓለም አቀፉ ‘ኋይት ኩብ’ የሥነ-ጥበብ ማዕከል አባል ሆነ
19:55 07.08.2026 (የተሻሻለ: 20:04 07.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ የዓለም አቀፉ ‘ኋይት ኩብ’ የሥነ-ጥበብ ማዕከል አባል ሆነ
ሠዓሊው ማዕከሉን መቀላቀሉንና ሥራዎቹን በ"ፍሪዝ ሴኡል 2026" የሥነ-ጥበብ ኤግዚቢሽን ላይ እንደሚያቀርብ ዓለም አቀፉ ‘ኋይት ኩብ’ የሥነ-ጥበብ ማዕከሉ አስታውቋል፡፡
በመቀጠልም ሠዓሊው ከጳጉሜ 4 2018 - ጥቅምት 10 2019 ዓ.ም በሆንግ ኮንግ በሚገኘው የኋይት ኩብ የሥነ-ጥበብ ማዕከል የመጀመሪያ የግል ዐውደ-ርዕይ ያቀርባል።
ስለ ሠዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ በጥቂቱ፦
🟠 እ.ኤ.አ. በ2024 በቬኒስ ቢናሌ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተወከለችበት ብሔራዊ ፓቪሊዮን ላይ ሀገሩን በብቸኝነት የወከለ የመጀመሪያው ሠዓሊ ነው።
🟠 በ2023 በ"አርትሲ ቫንጋርድ" ከተመረጡ የዓለማችን ተስፋ ሰጪ የጥበብ ሰዎች አንዱ የነበረ ሲሆን፤ ሥራዎቹ በኒውዮርክ ብሩክሊን ሙዚየም እና በፍሎረንስ ኡፊዚ ጋለሪ ጨምሮ በታዋቂ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ተካተው ይገኛሉ።
🟠 የሠዓሊው ሥራዎች የኢትዮጵያን የቅዱሳት ሥዕላት ባህል ከጀርመን የገለፃ ዘይቤ ጋር ያዋሃዱ ሲሆን፤ ስደት፣ የቤተሰብ ግንኙነት እና ማኅበራዊ ፍልሰትን የሚያንጸባርቁ ናቸው።
ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኘ ቪዲዮ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X