ኡጋንዳ የሀገሪቱን ጦር በዓለም አቀፍ የማረጋጋት ተልዕኮ አካል አድርጋ ወደ ጋዛ ለመላክ የቀረበውን የወሳኔ ሐሳብ አጸደቀች

ሰብስክራይብ

ኡጋንዳ የሀገሪቱን ጦር በዓለም አቀፍ የማረጋጋት ተልዕኮ አካል አድርጋ ወደ ጋዛ ለመላክ የቀረበውን የወሳኔ ሐሳብ አጸደቀች

የጦር ሰራዊቱ መላክ ከዩጋንዳ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታዎች እና ዓለም አቀፋዊ ቁርጠኝነቶች ጋር የሚጣጣም ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ ኡጋንዳ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሰላምን፣ ደህንነትን እና ትብብርን እንድታስፋፋ የሚያስገድዱ ናቸው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር ኪርዮዋ ኪዋኑካ ገልጸዋል።

የኡጋንዳ ህዝቦች መከላከያ ሰራዊት ስብስብ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 2788 (2025) እና በጥብቅ ሰብአዊ መርሆዎች ስር ይንቀሳቀሳል፡፡

▪ ገለልተኛ ሆኖ መቆየት፤

▪ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግን ማክበር፤

▪ ወገን ሳይይዙ ሲቪሎችን መጠበቅ፤

▪ በማረጋጋት ተልዕኮው ኃላፊነት ስር ብቻ መሳተፍ።

ፓርላማው ስምሪቱን ያጸደቀው ቢሆንም፣ በርካታ ሕግ አውጪዎች የውሳኔ ሀሳቡ የቀረበበትን መንገድ በተመለከተ ጥያቄ አንስተዋል፦

"ወታደሮቻችንን እስራኤል በተደጋጋሚ ጥቃት እንደምትሰነዝርበት እንደ ጋዛ ወደተለየ ከፍተኛ አደጋ ያለበት ቦታ የመላክ ጉዳይ እዚህ እንዲያው በቀላሉ የሚያልፍ አይደለም። በበቂ ሁኔታ መዘጋጀት አለብን" ሲሉ የፓርላማ አባል ፓትሪክ ንሳምባ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0