ታንዛንያ እና ኡጋንዳ የምሥራቅ አፍሪካን አዲስ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopiaታንዛንያ እና ኡጋንዳ የምሥራቅ አፍሪካን አዲስ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
ታንዛንያ እና ኡጋንዳ የምሥራቅ አፍሪካን አዲስ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.08.2026
ሰብስክራይብ

ታንዛንያ እና ኡጋንዳ የምሥራቅ አፍሪካን አዲስ የኃይል ማዕከል ለመገንባት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ 

​ሁለቱ ሀገራት የታንዛንያን የታንጋ ወደብ ከነባሩ የላኪነት ሚናው በማሳደግ፣ አጠቃላይ የቀጣናው የኃይል ማዕከል ለማድረግ "ከቪቶል ባህሬን"  ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

​🟠 የኡጋንዳ የድፍድፍ ነዳጅ የውጭ ንግድ ግንባታው ሊጠናቀቅ የተቃረበውንና 1,443 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የምሥራቅ አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር የሚጠቀም ሲሆን፣ የታንጋን ወደብ የዓለም አቀፍ ገበያ መውጫ በር ያደርገዋል።

​🟠 ማዕከሉ የነዳጅ ማከማቻን፣ የነዳጅ ማቀላቀያን፣ የባህር ላይ አገልግሎቶችን፣ ሎጂስቲክስን እና የኢነርጂ ንግድን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፣ ይህም የአፍሪካ ሀገራት በውጭ ሀገራት የነዳጅ ማጣሪያና ንግድ ማዕከላት ላይ ከመደገፍ ይልቅ ከሀብታቸው የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

​🟠 ፕሮጀክቱ በናይጄሪያው ዳንጎቴ ሞዴል የሚገነባውን የቀጣናዊ ነዳጅ ማጣሪያ እቅድ የሚያግዝ እና የሚያሟላ ነው።

​🟠 በዚህምፈ ስምምነት ታንዛንያ የሥራ እድልን፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን እና የሎጂስቲክስ ማዕከልነትን የምታገኝ ሲሆን፤ ወደብ አልባዋ ኡጋንዳ ደግሞ አስተማማኝ የውጭ ንግድ መውጫ እና ዝቅተኛ የትራንስፖርት ወጪን ታረጋግጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0