ከ91 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮችን የሚያስጠቅመው የመልሶ ማልማት እርሻ ዘዴ የሙከራ ትግበራ
15:05 07.08.2026 (የተሻሻለ: 15:14 07.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከ91 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮችን የሚያስጠቅመው የመልሶ ማልማት እርሻ ዘዴ የሙከራ ትግበራ
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሚገኙ አነስተኛ አርሶ አደሮች ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ እና ከጃፓን መንግሥት በተገኘ ድጋፍ የምግብ ምርታማነትን የሚጨምር እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አዲስ የመልሶ ማልማት እርሻ ዘዴ በሙከራ ላይ እያዋሉ ይገኛሉ።
በፕሮጀክቱ፣ በኢትዮጵያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ሴቶችን ጨምሮ ከ91 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ ገልጿል።
በዚህ ፕሮጀክት አርሶ አደሮች የሚከተሉትን ጥቅም ላይ አውለዋል፦
"ኢ-ካካሺ" የተሰኘ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚሠራ የዲጂታል ግብርና ቴክኖሎጂ፣
የቨርሚኮምፖስት እና ባዮቻር አፈር ማሻሻያዎችን እንዲሁም የተቀናጁ አሰራሮች
የአፈር አሲዳማነትን ማከም፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ አጠቃቀም፣ የአፈር ካርቦን ማደስ እና
አነስተኛ እርሻ ማረስ ዘዴዎችን ከዲጂታል የመረጃ ትንተና ጋር ማዋሃድ።
በሙከራ ማሳዎች ላይ የስንዴ ምርት በሄክታር በ89% (ከ1,293 ኪ.ግ ወደ 2,443.7 ኪ.ግ) ያደገ ሲሆን፤ የበቆሎ ምርት ደግሞ በ272% (ከ1,222 ኪ.ግ ወደ 4,541.8 ኪ.ግ) ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X