- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የኢንሹራንስ ዘርፍ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ጽናት ያለው ወሳኝ ፋይዳ

የኢንሹራንስ ዘርፍ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ጽናት ያለው ወሳኝ ፋይዳ
ሰብስክራይብ
በአብዛኛው የኢንሹራንስ አገልግሎት ከጉዳት በኋላ የሚደረግ ማካካሻ ተደርጎ ይታሰባል። ነገር ግን የኢንሹራንስ ዘርፍ ከዚህም በላይ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ምሰሶ በመሆን ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
"በአፍሪካ ያለው የኢንሹራንስ ዘርፍ አሁን ካለበት የካሳ ክፍያ ብቻ ላይ የሚያተኩር አቀራረብ ወደ የጽናትና የመቋቋም አቅም ኢንቨስትመንት የሚያተኩር ሥርዓት መሸጋገር ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የአስተሳሰብ ለውጥ በጣም ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ተቋማት ይህንን የጥበቃ ክፍተት ለመሙላት አዳዲስ የንግድ ሞዴሎችን እየተገበሩ ነው። ለምሳሌ፣ በአፍሪካ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ አደጋዎች የሚደርሱ ኪሳራዎች ውስጥ በኢንሹራንስ የሚሸፈነው 0.5 በመቶ ብቻ ነው። በአደጉ ሀገራት ግን ይህ ቁጥር 50 በመቶ ይደርሳል። ስለዚህ ከአየር ንብረት ነክ አደጋዎች አንፃር በአፍሪካ እጅግ ሰፊ የኢንሹራንስ ጥበቃ ክፍተት እንዳለ ይህ በግልጽ ያሳያል።" ሲሉ ፍቅሩ ጸጋዬ በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የስትራቴጂና የቢዝነስ ልማት ዋና ኃላፊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የ ኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን በክፍል አንድ ኢንሹራንስ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ጽናት እንዴት ስትራቴጂያዊ ምሰሶ ሊሆን እንደሚችል እንቃኛለን። በክፍል ሁለት ደግሞ የአፍሪካ ን ስልጣኔ እና በዓለም አስተዳደር ያላትን ሚና አእና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሱሌማን አንታ ንዲያይ ፣ የአፍሪካ አንድነትና ሉዓላዊነት አቀንቃኝ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝ ናከዲ ምባባማ አነጋግረናቸዋል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0