በኢትዮጵያ አዲስ የሞለኪዩላር ቲቢ ምርመራ ማሽኖች ይፋ ተደረጉ

ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ አዲስ የሞለኪዩላር ቲቢ ምርመራ ማሽኖች ይፋ ተደረጉ

አዲሱን ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ይፋ አድርገውታል፡፡

 

ተንቀሳቃሽ የሆነው አዲሱ ቴክኖሎጂ፦

የቲቢ (የሳንባ ነቀርሳ) በሽታ ምርመራን የሚያሻሽሉ እና የሚያፋጥን ነው፡፡

 

በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች፣ በማረሚያ ቤቶች፣ በማዕድን ማውጫዎች እና በአርብቶ አደር አካባቢዎች ለሚኖሩ ማኅበረሰቦች የምርመራ አገልግሎት ተደራሽነትን በእጅጉ ያሳድጋል።

 

በመጀመሪያው ምዕራፍ 268 የሞለኪዩላር ቲቢ ምርመራ ማሽኖች በ134 ጤና ጣቢያዎች ይገጠማል፡፡

በቀጣይ ተጨማሪ 3,000 የምርመራ ማሽኖችን በመግዛት በመላ አገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቋል።

 

ቴክኖሎጂውን በብቃት ሥራ ላይ ለማዋል ለጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0