ኢትዮጵያ እና ቤኒን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
16:15 06.08.2026 (የተሻሻለ: 16:24 06.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቤኒን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
በቤኒን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አድርጓል።
ሁለቱ ሀገራት በሚከተሉት ዘርፎች ላይ በጋራ ለምሥራት ፍላጎት እንዳላቸው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
በቴክኖሎጂ ሽግግር፣
በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና
በአቅም ግንባታ
ሀገራቱ በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ተመሳሳይ ራዕይና ጉዞ ያላቸው በመሆኑ በጋራና በትብብር መሥራታቸው ዘላቂ ልማት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው መግለጻቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X